አዎ ዶ/ር አብይ ይከሰሱ፤ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ጥሪ

አዎ ዶ/ር አብይ ይከሰሱ፤ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ጥሪየመብት ተሟጋቹ ያሬድ ኃይለማርያም በእርግጥም ዶ/ር አብይ ይከሰሱ እያለ ነው እንዴት ያንብቡት ሼር ያድርጉትዶ/ር አብይ መከሰስም ሆነ መወቀስ ካለበት በወጣት ህሊና ግጥም ሳይሆን ህብዝን ሲያሸብሩ፣ የእርስ በርስ ግጭቶችን ሲቀሰቅሱ እና የመንግስት አካላት ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ እንቅፋት የሆኑት እነ ጃዋር መሃመድን እና ግብረ አበሮቹን በሕግ ተጠያቂ ባለማድረጉ ነው። እነዚህ ሰዎች ጥላቻን በአደባባይ ሲሰብኩ፣ እነሱ በቀሰቀሱት ሁከት የሰው ህይወት ሲጠፋና ንብረት ሲወድም እያዩ ከልክ ባለፈ ትዕግስት ሲያስታምሙ በመቆየታቸው ሊጠየቁ ይገባል። በተቃራኒው ሃሳባቸውን በጨዋ ደንብ በማንጸባረቃቸው ብቻ በባለአደራ አባላት እና አመራር ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ፤ ከዛም አልፎ እንደ ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩን አይነት ሰላም ሰባኪዎችን በማሰራቸው ሊጠየቁ ይገባል።ህሊና በግጥሟ ውስጥ ያንጸባረቀችውን ሃሳብ መቃወምም ሆነ መንቀፍ፣ መተቸት ይቻላል። ግጥም እና እረቂቅ ሚስጥር የያዙ ስዕሎች ሁሌም ለብዙ እይታዎች እና ትርጉሞች ክፍት ናቸው። ገጣሚውም ሆነ ሰዓሊው ባላሰቡት መልኩ ሁሉ አንባቢና ተመልካች ሊተረጉማቸው ይችላል። የእነዚህ ኪነ ጥበባዊ ሥራዎች ውበትም ይሄው ነው። ከዛ አልፎ ግን ገጣሚዋን ማንቋሸሽ፣ የጥላቻ ስሜት ማንጸባረቅ፣ ስድብ እና ዛቻው ግን ህሊና ቢስ ከሆነ ሰው የሚጠበቅ አስነዋሪ ተግባር ነው።ይች ልጅ በግጥሟ ውስጥ ማንንም ሰው ወይም ቡድን ወይም ማህበረሰብ በስም ጠርታ አላመሰገነችም፣ አላንጓጠጠችም፣ አላወገዘችም። በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ሊንጸባረቁ የሚችሉ የሰዎች እና የቡድኖች ባሀሪያትን ግን ቁልጭ አድርጋ አስቀምጣለች። መጥፎ የሚባሉ እሳቤዎችን አውግዛለች፤ ጥሩውን አወድሳለች። እራሳችንን የቱጋ እንደቆምን መፈለግ የኛ ድርሻ ነው። መጋ፣ ዘረኛ፣ ጎጠኛ፣ ጠባብ ነኝ ያለ በመንጋ ተርታ፤ መልካም አሳቢ፣ አገር ወዳድ፣ ወገን አፍቃሪ እና ሁሉን አቃፊ፣ የራሱን ብሔር ከሌሎች የማያስበልጥ ወይም የማያሳንስ እና በእኩልነት መንፈስ የታነጸ ሰው ነኝ ያለ በመልካሞች ተርታ እራሱን ያሰልፍ። እዳው ለራስ እንጂ ወደ ገጣሚዋ የሚሔድበት ምንም አግባብ የለም። የልጅቷን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ለማፈን የሚደረገው ጥረት ግን ውጉዝ ከማሪዎስ ሊባል ይገባዋል። የህሊና አይነት ሃሳባቸውን በድፍረት፣ በአማረ ቋንቋ እና ልዩ ጥበብ መግለጽ የሚችሉ ባለህሊና ወጣቶችን ያበርክትልን።አቶ ግርማ ጉተማ ልጅቷም ሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕግ ይከሰሳሉ የሚል ነገር ጠቅሰዋል። ይቺ የሳምንቱ አስቂኝ ንግግር ተደርጋ ትወሰድ። የማን ስም ጠፋ ተብሎ ይሆን ክስ የሚመሰረተው? እርሶ እኳ አንድን ማህበረሰብ እና የአንድ እምነት ተከታት በተደጋጋሚ ጊዜ በስም እየጠሩ ሲሳደቡ፣ ሲያንቋሽሹ፣ እርምጃ እንዲወሰድበት ሲቀሰቅሱ በሕግ የጠየቀዎት የለም። ዶ/ር አብይ እርሶን፣ ጃዋርን እና መሰል ጥላቻን እና አመጽ ቀስቃሽ ንግግሮችን የምታደርጉትን ሰዎች ሳይከሱ ህሊና ትከሰስ ማለት ህሊና ቢስ መሆን ብቻ ነው የሚጠይቀው።
ያሬድ ኃይለማርያም

ሰበር ዜና

+++ ሰበር ዜና +++
መስከረም 4/2012 ዓ.ም ሊያካሄድ ስለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በአስተባባሪ ኮሚቴው በኩል መግለጫ ተሰጠ።
የሰልፉ አስተባባሪዎች ከአፋር እና ከትግራይ ክልል በስተቀር ከሁሉም ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች እና የጸጥታ ኃላፊዎች ጋር ቤተክርቲያኒቱ በገጠሟት ችግሮች ዙሪያ ሠፊ ውይይት አድርገዋል::
ቤተክርስቲያኒቱ እና ምእመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እና መከራ አስረድተዋል:: የሰልፉም ዓላማ ይሄው ነበር:: ለቤተክርስቲያንም ይህ ትልቅ ድል ነው:: በቀጣይም
1)በዐሥር ቀን ውስጥ ከኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሶማሌ፣ ድሬዳዋ፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ክልሎች አመራሮች ጋራ ውይይቱ ተጠናክሮ ችግሮቹን መፍታት በተግባር እንዲጀመር፤
2)ይህም ተፈጻሚነት እስከ ጥቅምት 30 ታይቶ ካልኾነ ሰላማዊ ሰልፍ እንደገና እንዲጠራ፤
3)አፈጻጸሙን በተመለከተ ቢያንስ በየ15 ቀን መግለጫ እንዲሰጥ፤
4)ሌሎችንም የእምነት ተቁዋማት ያሳተፈ ሰፋፊ የአዳራሽ ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች እንዲዘረጉ
በሚሉት አካሄዶች ላይ ከስምምነት ተደርሷል::

እንግዲያውስ ሕዝብ ይወቅ!

እንግዲያውስ ሕዝብ ይወቅ!

አዴፓ በ2011 ዓ/ም መጀመርያ ወራት ባደረገው ስብሰባ አንድ ድክመቱን አመነ። ከሌሎች በባሰ ብአዴን/አዴፓ ስለ ክልሉ ሕዝብ የረባ መረጃ አይደርሰውም። ትህነግ/ሕወሓት በጎንደር፣ ኦነግ በወሎና በሸዋ የአማራን ሕዝብ ሲያምስ አዴፓ/ብአዴን መረጃ አልነበረውም። ቀድሞ መተንበይ፣ መተንተን፣ መከላከል የሚችልበት መረጃና የመረጃ ስርዓት አልነበረውም። ሌሎቹ አልፈው ሲያጠቁ አዴፓ ግን የአማራ ሕዝብ ላይ ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ በሚዲያ ነበር የሚሰማው። ያም ሆኖ የሚረባ እዝ ስላልነበር መፍትሔ ለማምጣትም ሲከብድ ታይቷል። አዴፓ ይህን ድክመቱን አምኖ፣ ከሌሎች ክልሎች እጅግ ያነሰም ቢሆን መረጃ የሚሰበስቡለት ሰዎች መኖር እንዳለባቸው አመነ። ይህን ለመስራት ዋነኛው ሰው ኮ/ል አለበል አማረ እንደሚሆን አምኖ የቤት ስራ ሰጠው።

ኮ/ል አለበል ይህን ስራ ከውኗል። ሰራተኞቹን አሰልጥኗል። ተመርቀው ወደ ስራ ሊገቡ አንድ ወር ሲቀራቸው የሰኔ 15ቱ ክስተት አደናቀፈ። እነ ኮ/ል አለበል ይሰሩት የነበረው ስራ ከዚህና ከዚህ ጋር የተያያዘ ብቻ ነበር። ይህኛውን ስራ እየከወኑም ቢሆን ግን ላይ ታች ይሉ ነበር። በዚህ ወቅትም ወደ ከሚሴና ሸዋ እየሄዱ ጥቃት ሲከላከሉ ቆይተዋል። ሰኔ 15/2011 ዓ/ም ችግር ሲፈጠርም እነ ኮ/ል አለበል ከዚሁ አካባቢ እንዲመለሱ ተደርገው፣ መግለጫ እንዲሰጡ ተደርገው ነው የታሰሩት።

እነ ኮ/ል አለበል ስራ የአማራን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነበር የሰሩት። ሆኖም ከሰኔ 16 ጀምሮ ለእስር ተዳርገዋል። እነ ኮ/ል አለበል የክልሉን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ያሰለጠኗቸው የመረጃ ሰራተኞች (በርካታ ሚሊዮን ብር ፈስሶ) እንዲበተኑ ተደርጓል። በእስር ላይ የሚገኙም አሉ። እነዚህ ሰራተኞች ስልጠና ወስደው ገና ስራ እንኳን ባልገቡበት “አሳምነው ያሰለጠናቸው ናቸው” ተብለው ለእስር ተዳርገዋል። በመረሰቱ እነዚህ ሰልጣኞች ስራ አልጀመሩም። እነዚህን ልጆች ያሰጠኗቸው ሰዎች ከሰኔ 15 በኋላም የሌሎች ክልሎችን መረጃ ሰራተኞች አሰልጥነዋል።

(ይህን ጉዳይ የምፅፈው የፌደራል መንግስቱም፣ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችም ሌሎችም የሚያውቁት በመሆኑ ነው። እንዲያውም ተለጥጦ እነዚህ ሕዝብ ላይ የሚፈፀምን ጥቃት የሚከላከሉ ሰልጣኞች ለሌላ አላማ እንደሚሰለጥኑ ተደርጎ ሪፖርት ሲፃፍ ከርሟል። በአንፃሩ ሕዝብ መረጃ ላይኖረው ይችላል በሚል ነው።)

እነ ኮ/ል አለበል ለዚህ ስራ ወደ ክልል ከመጡ ጀምሮ ደስተኛ ያልሆኑ አመራሮች እንደነበሩ ይታወቃል። ሰኔ 15ን እንደ አጋጣሚ ተጠቅመው እነ ኮ/ል አለበል አማረንና የተወሰኑ ሰልጣኞችን አስረው ሌሎቹን በትነዋቸዋል። ሰልጣኞቹ ከፖለቲካ ነፃ ሆነው ከተለያዩ አካላት የተውጣጡ የነበሩ ሲሆኑ አንዳንድ የአዴፓ ሰዎች ይህን ለሕዝብና ለሕዝብ ብቻ ይሰራል ተብሎ የተገመተ ኃይል የፈለጉት አይመስሉም። በሰኔ 15 ሰበብ የታሰሩት አንዳንድ ሰልጣኞች ሲፈቱ ሌሎቹ በእስር ላይ ናቸው። የአማራ ሕዝብ ጥቃት ላይ ሆኖም ቀሪዎቹ እንዲበተኑ ሆኗል።

እነ ኮ/ል አለበል ከታሰሩ ጀምሮ ማስረጃ አልመጣባቸውም። እንዲያውም ከሰኔ 15 ግድያ በተአምር የተረፉ ሰዎች ናቸው። “ከተፈቱ ይለይልናል” የሚል የአማራውን ብርታት የማይፈልግም እንዳለ እየሰማን ነው።

እነ ኮ/ል አለበል ላይ የምትቀርበው አንድ ነገር “ችግር እንደሚከሰት እያወቁ ሪፖርት አላደረጉም” የሚል ነው። ይህ እነሱን ሆን ብሎ በእስር ላይ ለማቆየት የመጣች ምክንያት እንጅ ችግር እንደነበር ይታወቅ ነበር። አይደለም የአዴፓ ከፍተኛ አመራር ይቅርና ከተማው ውስጥ ብዙ ሰው የሚያውቀው ችግር ነበር። አዴፓ ከሁለት ጊዜ በላይ ስብሰባ ተቀምጦ ጉዳዩን ለማርገብ ሞክሯል። “ፋኖ ይውደም” ተብሎበታል የተባለው ስብሰባ አንደኛው ነበር። ሰኔ ወር መጀመርያ አቶ ምግባሩ ከበደ መወያያ ፅሁፍ አቅርቦ የተወያዩበት ሌላኛው ነበር። እነ አለበል “ሪፖርት አያደርጉም” የተባለውም ከእውነት የራቀ ነው። የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ችግር መኖሩን አውቀው ምክክር እንዲደረግበት ጥረት ያደረጉበትን ሁሉ ማስታወስ ተገቢ ነው። በዚህ ጉዳይ እነ ዮሃንስ ቧ ያለው፣ መላኩ አለበል፣ ላቀ አያሌው ጉዳዩን የማያውቁት ሆነው አይደለም። ለአዴፓ አንድነት ሲባል ለአማራ ሕዝብ ዘብ የቆሙና መቆም የሚችሉት በእስር እንዲማቅቁ ሊፈረድባቸው አይገባም!

እነ ኮ/ል አለበል አማረ “ሪፖርት አላደረጉም የሚባለውን ማሞኛ ለሟች ቤተሰቦች ጭምር ለማስያዝ የተሞከረበት አካሄድ የሚያሳዝን ነው። አንድ ሰሞን የአዴፓ አመራሮች ራሱን ኮ/ል አለበልን ሽምግልና ልከው እንደነበር ሊያስታውሱት ይገባል።

ዋናው ነገር እነ አለበል አማረ የታሰሩት ከሰኔ 15 ጋር ግንኙነት ኖሯቸው አይደለም። ሰኔ 15 እንደሚከሰት የአዴፓ አመራር ጠፍቶት አይደለም። ከአዴፓ ጋር ግንኙነት የሌላቸው አካላትም ሽምግልና ለመላክ ጥረት ማድረጋቸው ሁሉ እናውቃለን። የአዴፓ አመራር ልዩነት እንደነበር ያውቅ ነበር። እነ ኮ/ል አለበልና ጄ/ል ተፈራ ማሞን በእስር ለማቆየት የሚፈልገው አመራር አማራ አንገቱን ቀና አድርጎ እንዳይሄድ የሚፈልግ ካልሆነ ሌላ ሊባል አይችልም።

አንዳንድ መረጃዎችን ይዘን ዝም የምንለው በክልሉ ላይ ያለው ችግር ከእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዳይሆንና ከዕለት ዕለት ይሻሻላል በሚል እንጅ ንፁሃንን ሲታፈኑ ዝም ልንል አይደለም።

የአዴፓም ሆነ የአማራው ሕዝብ ችግር የሚፈታው ሰኔ 15 የተፈጠረው ክስተት በገለለልተኛ አካል ተመርምሮ ሕዝብ እውነታውን ሲያውቅ ነው። ሆኖም የዚህን ክስተት ጉዳይ ምርምራ ይዞታል። ይህ ምርመራ እውነታውን ያወጣል ይሆናል የሚል ግምት የነበራቸው ሰዎች ነበሩ። በንፁሃን ላይ የሚደረው አፈና ግን በምርመራው ላይ ሌላ ጥላ የሚያጠላ እየሆነ ነው።

እነ ኮ/ል አለበል ለአማራ ሕዝብ መከታ የሚሆን ተቋም እንዳይመሰርቱ እንቅፋት ሲሆን የነበረና አጋጣሚውን ያገኘ አካል “ምርመራቸው በፌደራል መንግስቱ መታየት አለበት” እስከማለት ደርሷል። በፍርድ ቤት ጣልቃ እየገባ፣ ዳኞችንና ሌሎችንም እያዋከበ ይህን አላማውን ለማስፈፀም ጥረት እያደረገ ነው። እነዚህ አካላት ከዚህ ፀረ አማራ ተግባራቸው ካልተቆጠቡ የአማራው ፖለቲካ ሳንካ ሊገጥመው እንደሚችል መገመት አይከብድም!

ሕዝብ ግን ማወቅ አለበት። እነ ኮ/ል አለበል አማረ ወንጀል ሰርተዋል ከተባለ ያ ወንጀላቸው አማራን ከጥቃት ለመከላከል መጣራቸው ብቻ ነው! ይህን ደግሞ የሰሩት አዴፓ አምኖበት፣ በጀትም በጅቶላቸው ነው።

እነ ኮ/ል አለበል ከእስር መፈታት ብቻ አይደለም የሚገባቸው። ወደ ቦታቸው ተመልሰው የጀመሩትን ስራቸውን መከወን አማራውን ከጥቃት መከላከል ይገባቸዋል። ከየትም ስራቸውን ጥለውና ቤተሰብ በትነው ለአማራ ሕዝብ ደሕንነት ሲባል ስልጠና የወሰዱ አካላትም ከመሳደድና ከእስር ወጥተው ሕዝባቸው ሊያገለግሉ ይገባል። በስልጠናው ወቅት አንዳንድ ችግሮች እንደነበሩ ይታወቃል። ይህ ችግር ደግሞ የእነ አለበል አይደለም። የአዴፓ አመራር ነው። ይህን አስፈላጊ ከሆነ ሌላ ቀን የምንመለስበት ይሆናል። ሆኖም በስልጠናው ወቅት ችግር ነበር ከተባለም የሚስተካከለው ነገር ተስተካክሎ እነ አለበል ስራቸውን መቀጠል እንጅ ሰበብ እየተፈለገ በእስር ሊማቅቁ አይገባም!

የዘውግ ለውጥ እንጂ ለውጥ የለም !!!

የዘውግ ለውጥ እንጂ ለውጥ የለም !!!
=======================
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዘመነ ዮዲት ጉዲትና ከግራኝ አህመድ ባልተናሰሰ መልኩ በዘመነ ወያኔ ብዙ መከራዎችን አሳልፋለች የችግሩን ብዛትና ጥልቀት ለመናገር ለቀባሪው አረዱት እንዳይሆንብኝ ነገሩ የኦሮሚያ ቤተክህነት ልንመሰርት ነው ሲኖዶሱ ፈቀደም አልፈቀደም ከመመስረት ወደ ኋላ ዝንፍ የሚያደርገን የለም በማለት ለሲኖዶሱ የአንድ ወር ጊዜ ሰተናል ብለው መግለጫ መስጠታቸው በእምነቱ ተከታዮች ላይ የፈጠረው ስሜት ይህ ነው ተብሎ አይገለጽም ላለፉት ዘመናት ወያኔ የፖለቲካውን አቅጣጯ ለማስቀየርና ትግሉን ወደፊት ለማስኬድ ሲል በየጊዜው የተለያዩ የቤት ስራዎችን ለህዝቡ ለተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሚዲያዎች ይሰጣል ዛሬም እንደተለመደው በዘመነ አብይ አስተዳደር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ለመከፋፈል የተመሰረተ የሽብር ነጋሪት እያስጎሰመ በቤተክርስቲያን አባቶችና በእምነቱ ተከታዮች ምእመናን ላይ ተጽኖ እየፈጠረ ይገኛል።

በዘመነ አብይ የሁለት ዓመት እድሜ እንኳን ባልሞላው አስተዳደር ውስጥ ብዙ ቤተክርስቲያን ተቃጥለዋል ካህናት ታርደዋል ንዋየ ቅድሳት ተዘርፈዋል በእምነቱ ተከታዮች ላይ ድብደባ የመግደል ዛቻ እየተፈፀመባቸው ይገኛል ይህ ሁሉ ሲደረግ የአብይ አስተዳደር በቤተክርስቲያኗና በምእመናን ላይ የሚደርሰውን አደጋ አለመከላከሉና ጥበቃ እንዲደረግ አለማድረጉ ምን ይህል ለእምነቱ ያለውን ቦታ ያሳያል እንደው በአደባባይ እየወጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐይማኖት ሀገር ነች ክብራችን ነች እያሉ ማላዘኑ በሐይማኖትና በእምነቱ ተከታዮች ላይ መቀለድ ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እርሶ እንዳሉት ሀገር ብቻ ሳትሆን ከሀገር ትልቃለች ኢትዮጵያ እንደ ኢትዮጵያ ሆና እንድትቀጥል ሀገሯንና ዳር ድንበሯ እንዲከበር ወራሪን ጠላት በመመከት ለስልጣኔ በር ከፋች በመሆን ለአፍሪካና ለዓለም ብርሃን የሆነች ናት እንዲሁም ክማይነጥፈው ዘላለማዊ በረከቷና ሰማያዊ ሕይወትን የምታሰጥ ስንዱ ቤተክርስቲያን ነች አሁንም ወደፊትም በዚሁ ስራዋ ትገፋበታለችም ትቀጥላለች ቤተክርስቲያንን ማቃጠል ካህናትን ማረድ ምእመናንን ማሳደድ ከንቱ የከንቱ ድካም ነው ምክንያቱም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ደም ነው የተመሰረተችው ሊቁ ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ ስለ ቤተክርስቲያን እንዲህ ብሏል “ሰውን ብትታገልና ብትዋጋ ታሸንፈዋለህ፤ወይም ያሸንፍሃል፤ ቤተክርስቲያንን ግን ማሸነፍ አይቻልም፡፡ ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ ትዋጋለች፤ተሸንፋም አታውቅም፡፡ዲያብሎስ ዝናሩን አራገፈ ቀስቱን ጨረሰ ቤተክርስቲያንን ግን አልጎዳትም፡፡”

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰው ልጅን በዘሩ፣ በቋንቋው፣ በባሕሉ፣ እና በሀገሩ የተለያየ ማንነት ቢኖረውም ሁሉንም በአንድ አይን የምታይ ናት የሐይማኖቱ ማንነት ከሁሉ የበለጠ ማንነት ነው ብላ ታስተምራለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታዮች ለሐይማኖታቸው ቀናዒና ሰማዕት የሚሆኑ ናቸው ታሪክም እንደሚነግረን ብፁ አቡነ ጴጥሮስ ለሀገራቸውና ለሐይማኖታቸው ሰማዕተ ጽድቅ ዘ ኢትዮጵያ የሆኑ አባት ናቸው ወደ ቀደመው ነገር እንመለስና መንግስት ወደ ፖለቲካ ስልጣን ለመውጣት ከሚጠቀምባቸው ተቋማት አንዱ ቤት እምነት ቦታዎች ነው ለዚህም ዋናዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነች በዚች ቤተክርስቲያን ውስጥ የእምነት ተከታዮች ብዛት በግምት ክ55–60ሚሊዮን የሚኖሩ ተከታዮች ይኖራሉ ይህን አሃዝ ከምን አግኝተኅው ነው ያስቀመጥከው ካላችሁኝ መነሻዬ በግምት ያልኩ ሲሆን ካነሰ ደምሩበት ከበዛም አባዙት ዳግማዊ ወያኔ ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘትና የድርጅቱን አላማ ለማራመድ ሲል ለዚህም በቂ ድጋፍ ለማግኘት ዋና ምርጫው አድርጎ የተነሳው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ነው ይኅውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሁለት ሲኖዶስ መከፈል ምክንያት በተደጋጋሚ ሲወያዩና ሲደራደሩ ነበር ይህ ውይይት ለመገባደድ የ አንድ ቀን ዕድሜ ስብሰባ ሲቀረው ዶክተር አብይ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ስማቸውንና ዝናቸውን ለማትረፍ በዚህ የእርቅ ጉባኤ ላይ የተገኙት እናም ምን ያህል በኦርቶዶክስ እምነት ዘንድ ቦታ ማግኘታቸው ያመለክታል እናም ያሰቡትና ያቀዱት ሃሳብ ተሳካላቸው ቅዱስ ሲኖዶሱን አንድ እንዲሆኑ ካደረጉት አንዱ ተብሎ የሳቸው ስም በሰፊው ይወራል ይዘከራል ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው የሁለቱ ሲኖዶስ አንድ የመሆን ጉዳይ በፈቃደ እግዚአብሔር የሆነ ብቻ ነው ዶክተር አብይ ለቤተክስቲያኗ በመቆርቆር በማስመሰል ለፖለቲካ ፍጆታ ተጠቀመባት እንጂ በሱ የስልጣን ጊዜ ቤተክርስቲያን አንዳችም ነገር አልተጠቀመችም እንደውም በዘመነ አብይ አንድነቷና ሰላሟ እንዲናጋ ዳርጓታል ስለ ዶክተር አብይ ሎሬት የትነበርሽ ስትናገር እንዲህ ብላ ነበር ዶክተር አብይ የመጽሀፍ ቅዱስ ጠቅሶ ቢነግራችሁ እንኳን አትመኑት ምክንያቱም ፖለቲከኛ ነው።

ወያኔ በኢትዮጵያዉያን ብሄረሰቦች መሃከል የዘራዉ የጥላቻ መርዝ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት በኦሮሞና በአማራ ብሄረሰቦች መሃክል የመለያየትና የጎሪጥ እንዲተያዩ በማድረግ የጥላቻ ግንብ ገንብቶልናል ይህንን ግንብ በማጠናከር ዳግማዊ ወያኔ ኦሕዴድ የብሄር ተኮር ፖለቲካን የሚያራምድ የተረኝነት ስሜት ያደረባቸው የገዢውን መንግስት ሃሳብና ዓላማ የሚያራምዱ የኦሮሚያ ቤተክህነት እንዲመሰረት ጥያቄ ባነሱት ግለሰቦች ጀርባ ራሳቸውን የፖለቲካ ሊሂቃን ነን ብለው የሚያስቡና አክቲቪስት ነን ባዮች ጽንፈኞች ከሐይማኖት ቋንቋን የሚያስቀድሙ የወረደ አስተሳሰብ ያላቸው የተረኝነት ስሜት ያደረባቸው ፅንፈኛ አካሎች አሁን በማን አለብኝነት ተወጥሮና ገዝፎ የሚታየውን ከቋንቋ ማንነት አልፎ ወደ ዘርና ብሄር ተኮር እየሆነ ሀገራችንን አደጋ ውስጥ እየክተታት ይገኛል ይኅው ሰሞኑን እንዳየነው በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ሃሳብ (idology) ቋንቋን ብቻ ሳይሆን ብሔርን፥ሐይማኖትን፥ሀገርን፥ አንድነትን ያፈርሳል ለዚህም የኦሮሞና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም አክቲቪስት ነን ባዮች ለአማርኛ ቋንቋ ያላቸውን ጥላቻ በጉልህ ማሳየታቸው የሕብረተሰቡን መብት እኛ ብቻ እናውቅልሀለን ማለታቸው አምባገነናዊ ስርዓታቸውን አሳይተውናል ሐይማኖትን ከቋንቋና ከብሄር ማገናኛት በጣም ትልቅ ስህተት ነው ዳግማዊ ወያኔ የሚያራምደው ፖሊሲ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ላይ ላለንበት ቀውስ ከቶናል የአማርኛ ቋንቋን እንደ ጠላት ሊታይበት የቻለበት ምክንያት ምንድን ነው ምክንያቱም የሀገሪቷን ሕዝብ በዚህ ቋንቋ ያስተሳሰረ ስለሆነ ነው።በተጨማሪ አማርኛን ቋንቋ የአማራ ቋንቋ ነው ብሎ ማሰቡ አሁን ላለንበት ለማሰተማርና የሐይማኖት አንድነትን ለመከፋፈል እንቅፋት እየሆነ እንዳለ ማሳያ ነው ኢትዮጵያ ሀገራችን ከሌሎች ሀገራት ልዩ የሚያደርጋት የራሷ የሆነ ፊደል ያላት እንዲሁም የራሷ ቁጥር ያላት ሀገር ናት ያለንን በአግባቡ ካልተጠቀምንበት የራሳችን ነው ብሎ ከማውራትን የዘለለ ትርጉም የለውም።ቋንቋ መማር የሉዓላዊ ጉዳይ ነው ይህ ማለት እያንዳንዱ ቤተሰብ የሚጠቅመውንና የሚጎዳውን ነገር ለልጆቻቸው የሚወስኑት እነሱ ብቻ ናቸው እንጂ የክልል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የፖለቲካ ሊህቃን ነን ባዮችና አክቲቪስት ነን ባዮች የሚፈቅዱልህም ሆነ የሚከለክሉህ አይደሉም በሌሎች ሰዎች ላይ ሕይወት መወሰን ፈጽመው አይችሉም!!!

ዳግማዊ ወያኔ ኦህዴዳዊ ተልኮ የሚያራምዱ የተረኝነት ስሜት ያደረባቸው የፖለቲካን ሊሂቃን አክቲቪስት ነን የሚሉ የኦሮም ፅንፈኞች የመሳሰሉት የሚያደርጉት ሀሰተኛ ንትርክና የተንሸዋረረ አመለካከታቸውን በተለያዩ አጋጣሚ በሚዲያ ቋንቋን መሰረት በማድረግ ህዝብንና ሐይማኖትን የመከፋፈል የጥላቻ ንግግራቸውን ሲያንቧርቁ ይገኛሉኢትዮጵያ የህዝቦች ሰባዊ መብት የሚከበርባት እኩልነት የተረጋገጠባት ሰላምና ብልጽግና የሰፈነባት ሃገር ሆና እንድትቀጥል ብቻ ነው የምንፈልገው ትላንት ህወሃት በህዝቡና በቤተክርስቲያን ላይ ያደረሰው በደል መቼም አንዘነጋውም ዛሬ ደግሞ የተረኝነት ስሜት ተፀናውቶአቸው በህዝብና በቤተክርስቲያን ላይ አደጋ እያደረሱ ይገኛሉ የትላንት ስርዓት ለመቃወም በአንድ ላይ እንደተነሳን የዛሬውን ስርዓት ዝም ብለን አናየውም እንታገለዋለን እንቃወመዋለን!!!

መስፍን ቁምላቸው ክስቶኮልም

መንግስት አልባዋ ሀገራችን በጣም ያሳዝናል

መንግስት አልባዋ ሀገራችን በጣም ያሳዝናል#ጅማ ማርያም ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል የተዘጋጀ ቤንዚን ነው ፤ ምዕመናንም እኛ እያለን ቤተክርስቲያናችን የሚነካ የለም በማለት በተጠንቀቅ ቆመዋልአሁንም እንላለን አህዛብ ከቤተክርስቲያናችን ላይ እጃችችሁን አንሱ!! ክርስትና እና ሚስማር በመቱት ቁጥር ይጠብቃልና!!

የወቅቱ “ሰርካለም ፋሲል”

የወቅቱ “ሰርካለም ፋሲል”
*********************
ጭካኔ ያስጨክነኛል! እስከምጨክን ግን ጊዜ እወስዳለሁ፡፡ጨካኝ ጭካኔን የመረጠበት አንዳች ምክንያት ይኖረው ይሆን መጨከን ብቻ መፍትሄ ሆኖ አግኝቶት ይሆን፣ጨካኝ በቆመበት ቦታ ሆኜ ባየው ካልጨከነ የሚበላሽ ነገር ይኖር ይሆን በሚል በጨካኝ ላይም ቢሆን ቶሎ ላለመጨከን ከደመነፍሴ ጋር እሟገታለሁ፡፡ይህን የማደርገው አንዴ ጭካኔ ከገባኝ ለመመለስ ስሜቴ እሽ ስለማይለኝ ነው፡፡ በህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የመጨረሻ ዘመናት በጨካኙ ላይ የመጨከን ደረጃ ላይ ደርሼ ነበር፡፡ይህ ስሜቴ የኢህአዴግ ባለስልጣን ቀርቶ አሽቃባጭ ደጋፊ ሳይ ጭምር ደስ የማይል ስሜት እንዲሰማኝ ያደርገኝ ነበር፡፡ እዚህ ደረጃ ላይ ያደረሰኝ የህወሃት መራሹ መንግስት የተከማቼ ጭካኔ ላይ አንድ ሁለት ቀን በማምነው የቪኦኤ ሬድዮ የሰማኋቸው ታሪኮች ናቸው፡፡
አንደኛው አንድ አባት የሶስት ልጆቻቸው ሬሳ እንደከሰል በማዳበሪያ ተጠቅልሎ በራቸው ላይ እንደቆመላቸው ሲናገሩ የሰማሁት ታሪክ፣ ሁለተኛው በማዕከላዊ የደረሰበት ሰቆቃ በፍርድቤት በሰው መሃል ልብሱን አውልቆ ሃፍረተ ሰውነቱን እስከማሳየት ያደረሰውን ታሳሪ ታሪክ ስሰማ እና ሶስተኛው ብዙዎቻችሁ የምታውቁትን እናትን የልጇ አስከሬን ላይ አስቀምጦ የመደበደቡ ታሪክ ነው፡፡ እነዚህ ታሪኮች ቀድሜ ካነበብኳቸው ጭካኔዎች ጋር ተደምረው ሰው ባልሆኑ ፍጡራን እየተመራን እንደሆነ ይሰማኝ ጀመረና ጥላቻየም ሰውን ሳይን የሆነ አውሬን የምጣላ እስኪመስለኝ ድረስ የመረረ ሆነ፡፡ በአውሬ የመሰልኳቸው ሰው መጥላት ዘና ብየ የምቀበለው ስሜት ስላልሆነ ነው፡፡
ለማንኛውም እነዚሁ ሰዎች ተሸሻልን ብለው፣የባሰባቸውም ከስልጣን ተባረው አዲስ ዘመን የመጣ፣ ጫፍ የወጣ ግፍም አንሰማም የሚል ተስፋ ነበረኝ፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ዛሬም ሰዎች በገፍ ታፍሰው ይታሰራሉ፣ለአንዱ የተፈቀደ ነገር ለሌላው ወንጀል ሆኖ እንትን ቲቪን ለምን መሰረትክ የሚል ነገር መመርመሪያ መስቀለኛ ጥያቄ ሆኖ መጥቷል፡፡ሰው ሊጠይቅ የሄደ ሰው እንኳን ማርያም አመጣችህ ተብሎ በዛው እስርቤት ይዶላል፡፡
ከዚህ ሁሉ ብሶ እያሳዘነኝ ያለው ግን የነፍሰ-ጡሯ የጀነራል አሳምነው ፅጌ ባለቤት የወ/ሮ ደስታ ነገር ነው፡፡ይህች ሴት ከታሰረች ሁለት ወር ሊጠጋት ነው፡፡የትኛውም ፍርድቤት ቀርባ ወንጀሏ ሲነበብ እና ስትከራከር አላየንም፡፡ክስ ተመስርርቶባት ወደ መደበኛ ማረሚያቤት አልተወሰደችም፡፡ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ታጉራለች፡፡ ከሁሉም በላይ ነፍሰጡር ነች፤የህክምና ክትትል ያስፈልጋታል፣ባሏን ያጣች ሃዘንተኛ በዛ ላይ ነፍሰ-ጡር ሴት ወንጀልሽ ይህ ነው ሳትባል እስርቤት መታጎሯ እጥፍ ድርብ ግፍ ነው፡፡
ከሴት ያልተወለደ የለም፤እናት የሆነ ሴት ሁሉ ደግሞ እርግዝናን እና የስሜቱን ክብደት ያውቀዋል፡፡የሰውን ልጅ ያክል ነገር በሆዷ የያዘች ሴት ስንት ወር ሙሉ ፖሊስ ጣቢያ ያጎሩ ግፈኛ የለውጥ አመራር ተብየ ወንዶች ከሴት የተወለዱ፣በሚስቶቻቸው በኩል እርግዝና ምን እንደሆነ የሚያውቁ ናቸው፤ሴቶቹ የለውጥ አመራር ነን ባዮች ደግሞ በየደረሱበት ስለ ሴት ልጅ መብት የሚቀባጥሩ፣ልጅ አርግዞ መውለድም እንዴት ያለ ጫና ያለው ነገር እንደሆነ የሚያውቁ ናቸው፡፡ግን ሁሉም የዚች ምስኪን ሴት ነፍስ አያሳስባቸውም፡፡ለአልጀዚራ ዶክመንተሪ ቃል ለማሳመር የምትለፋዋ ወ/ሮ መዓዛም ይህን ሳታውቅ ቀርታ አይደለም፡፡የግለሰብ ጉዳይ አይመለከታትም እንዳይባል ስለ ግለሰብ ሴት እስረኞች ያላትን ተቆርቋሪነት በአልጀዚራ ስታወራ አይቻለሁ፡፡ይህች ሴት ግን ነገስታት በክፉ አይን ስላዩዋት ብቻ ጆሮ ዳባ ትባላለች፡፡ይህን የመሰለ ጭካኔ የሚያስጨክን ሃገራዊ ፋይዳ ያለው ምክንያት የላቸውም-ተራ ጥላቻ እና ቂም በቀል እንጅ!
አንድም እናት በወሊድ እንዳትሞት የሚፈልጉት የጠላታቸው ሚስት እስካልሆነች ድረስ ነው፡፡ይህች ሴት ግን በሚታመነውም በማይታመነውም ስሙን ሲያክፋፉት ምን ያህል እንደሚጠሉት የሚሳያሳብቅባቸው የጀነራል አሳምነው ሚስት ነች! ስለዚህ አንድም እናት እንዳትሞት ከሚባልላቸው ሴቶች ውስጥ አይደለችም ፤ቢሻት ትሙት! ይህች ሴት በህወሃት መራሹ ዘመን እስርቤት አርግዛ እስርቤት ስትዎልድ ከሞት አፋፍ የተመለሰችውን ሰርካለም ፋሲልን የምትመስል የተረኛ አምባገነን መከረኛ ነች፡፡ፈጣሪ አብሯት ይሁን እንጅ ምን ይባላል?
በጣም የሚያሳዝነው ይህች ሴት ይህን ሁሉ መከራ የምታየው የአሳምነው ሚስት ስለሆነች ብቻ ነው፡፡ እንጅ የሰራችው ወንጀል ቢኖር አንቀፅ ተጠቅሶባት ስትከሰስ እንሰማ ነበር፡፡ይህ ጭካኔ የኢህአዴግ ሰዎችን አረመኔነት ፣ተበቃይነት እና ግብዝነት የሚያሳይ ነገር ነው፡፡ ነገሩ እነዚህ ባለጊዜዎች ምን ያህል ጀነራል አሳምነውን ይጠሉት እንደነበረም ያሳያል፡፡የፈለገ ቢጠሉት አሁን እሱ ሚስቱ መታሰሯን አውቆ የሚያዝንም መፈታቷን ሰምቶ የሚደሰት ሰውም አይደለም-ከአፈር በታች የሆነ በድን እንጅ! ነገሩ ሁሉ ሬሳ መበቀል ድረስ የሚሄድ ኢህአዴጋዊ ክፋት ነው፡፡ ከዚህ ሌላ አንድ ምስኪን ነፍሰጡር ሴት የሚጠሉት ሰው ሚስት ስለሆነች ብቻ አስሮ ማንገላታት ምን ይባላል?የዚች ሴት ጉዳይ የዛሬ ሳምንት በጋዜጣ ወጥቶ ስመለከት ቢያንስ የልጅቷን ሮሮ ሰምተው አንድ ነገር ያደርጉ ይሆናል በሚል ነበር ቀናትን የጠበቅኩት፡፡ግን ነገስታት ልባቸው ይራራ ዘንድ ተራ ሰው አይደሉምና በጭካኔያቸው ላይ ተመቻችተው ተኝተዋል፡፡ይህ የሰው የማይመስል ጭካኔ ኢህአዴግ የሚባል ወትሮም አስቀያሚነቱ የሚታየኝ ፓርቲ ምን ቢኳኩሉት የማያምር የአውሬዎች ስብስብ መሆኑን ይናገራል!